Showing posts with label የስብከት አገልግሎት. Show all posts
Showing posts with label የስብከት አገልግሎት. Show all posts

Thursday, November 15, 2018

ፈውስ በማን ነው?

 
ክፍል አንድ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው ዘጸ. 15-፡-27
ቃሉን የተናገረው አምላካችን እግዚአብሔር ነው፡፡ የጽሑፉ ዋና ዓላማ የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት በግልጽ ማስረዳት ነው፡፡ ትእዛዙን ብታደምጥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ በግብፃዊያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ ለሙሴ ነግሮታል፡፡ ፈውስ የሚለው ቃል ከበሽታ መዳን ጤናን ማግኘት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የማይታዘዝ ህዝብ ካለ በበሽታ ሊቀጣ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‹‹ባትሰሙኝ ትእዛዜን ሁሉ ባታደርጉ ሥርዓቴንም ብትንቁ፣ ፍርሐትን፣ ክሳትንም፣ ዓይናችሁንም የሚያፈዝ ሰውነታችሁንም የሚያማስን ትኩሳት አወርድባችኋለሁ ይላል›› ዘሌዋ. 26፡14-፡-16
ትእዛዙን የሚጠብቅ ካለግን… ህማም ሁሉ ካንተ ይርቃል የምታውቀውንም ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ ባንተ ላይ አይደርስብህም ብሎ ለሙሴ ነግሮታል፡፡ ዘዳ. 7-፡-15
በሽታ በተለያየ መንገድ ሊከሰት ይችላል፡፡ ንፅህናን ባለመጠበቅ ሊመጣ ይችላል፡፡ እራስን ለእግዚአብሔር ባለማስገዛትም ሊመጣ ይችላል፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ በበሽታ ከተቀጡ መካከል ስንመለከት፤-
1.እህተ ሙሴ ማርያም እግዚአብሔር ባከበረው በነብዩ ሙሴ ላይ የማይገባትን በመናገሯ እግዚአብሔርንም ባለመፍራቷ በለምጽ ተመትታለች፡፡ ዘኁል. 12፡-10
2.ነብየ እግዚአብሔርን ባለመታዘዙ ኤልሳ እየዋሸ የማይገባውን ንብረት በመውሰዱ የንዕማንን ለምፅ በዘሩ ላይ ተጣብቆበት የኖረ እንደበረዶም ለምጻም የሆነ ጊያዝን እንመልከት፡፡ 2ኛነገ. 5-፡-25-27
3.የቤተመቅደሱ አገልጋይ ካህኑ ዘካርያስ የእግዚአብሔርን መልክተኛ ባለመታዘዙ ከ275 ቀናት በላይ ድዳ ሆኖ ተቀጥቷል፡፡ ሉቃ. 1-፡-20
4.ሰርግዮስ የተባለ አገረ ገዥ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በፈለገ ጊዜ በርያሱስ የተባለ ጠንቋይ አገረ ገዥውን እንዳያምን የእግዚአብሔርንም ቃል እንዳይሰማ ጳውሎስንና በርባናስን ተቃወማቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሳውል የተባለ ጳውሎስ ተንኮል፣ ክፋት የሞላብህ የጽድቅም ጠላት ስለሆንክ ዓይንህ አይይ አለው፡፡ ዓይኑም ታወረ ጽድቅን በመቃወሙ ታመመ፡፡ ሐዋ. 13-፡- 11

Wednesday, September 26, 2018

ወገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ

ወገብረ ሰላመ  በደመ  መስቀሉ <<በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደሙ ሰላምን አደረገ>> ቆላ. 1-፡-20

 

መስቀል በቀደመ ዘመን ለኃጢአተኞች እግዚአብሔርን ለበደሉ መቅጫ የነበረ ነው፡፡ በእንጨት ላይ የተሰቀለም በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፡፡ ኦ/ዘዳ 21፡23 በሐዲስ ኪዳን ግን ለክርስቲያኖች ኃይል  ጽንዕ ቤዛና መድኃኒተ ነፍስ ሆኖ የሚያገለግል ዓርማ ነው፡፡ መስቀል የምንለው በቁሙ ከቤተክርስቲያን ጉልላት እስከ ምዕመናን ንቅሳት የሚታይ የድል ምልክት የደህንነት ዓርማ (ምልክት) የክርስቲያኖች የማንነት መገለጫ    የተጋድሎ ፍኖት ነው፡፡ 1ጴጥ. 2፡21                          
የክርስቶስ  መስቀል ለምናምን  ለኛ  ፡- የጥል ግድግዳ የፈረሰበት  ሰላማችን ነው  ኤፌ 2፡14 ሰው እንጨት ቆርጦ ቢበላ አምላኩን በደለ የፀብ ግድግዳም ተተከለ  ሰው ከአምላኩ ተለየ፡፡ ‹‹ለያይቶን የነበረውን የጥል ግድግዳ ያፈረሰና አይሁዳዊያንና አሕዛብን አንድ ያደረገ ሰላማችን ክርስቶስ ነው›› እንዲል: : ከእርሱ ጋር የታረቅንበት ኃይላችን ነው በመስቀል ላይ በመሞት ጠላትን አስወገደ ሁለቱንም አንድ አካል አድርጎ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ እንዲል ኤፌ. 2፡16 ጠላታችን የራቀበት እኛ የቀረብንበት ጋሻችን ነው፡፡ የቀደመው እባብ የዲያብሎስን ራስ የተቀጠቀበት እኛም ድል መንሳትን በግለጥ ያየንበት  ዕፀ መድኃኒት ነው፡፡ በእኛ የነበረውን የሚቃወመንንም በትዕዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ደበዳቤ ፅሕፈት ደመሰሰው እርሱንም በመስቀሉ ቸንክሮ ከመንገድ አስወገደው እንዲል ቆላ. 2፡14 ዐረፍተ ማዕከል የተናደበት የሕይወት ህብስት የተቆረሰበት ዕፀ መስቀል በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት በዓለ መስቀልን መከበር የተጀመረው ዛሬም በኢትዮጵያችንም በተለይ በግሸን ደብረ ከርቤ  ከአራቱ ማዕዘን በሚመጡ ምዕመናን በደማቅ ሁኔታ  እየተከበረ ይገኛል:: መስቀል በዓመት አምስት ጊዜ የሚከበር ሲሆን ይኸውም መስከረም 16 ቀን የደመራ በዓል ቅዳሴ ቤት መስከረም 17 ቀን ንግስት ዕሌኒ ቁፋሮ ያስጀመረችበት መስከረም 10 ቀን አፄ ዳዊት መስቀሉን የተረከቡበት አፄ ዘርዓ ያዕቆብ በደብረ ብርሃን ከተማ ያስገቡበት ተቀፀል ጽጌ ይባላል፡፡ መስከረም 21 ቀን 1446 ዓ.ም በግሸን ተራራ ያረፈበት በማስመልከት በየዓመቱ  እየታሰበ ይገኛል፡፡   በረከተ መስቀሉ  አይለየን!     

አድራሻ፡- ከቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተ/ክ ዝቅ ብሎ ያገኙናል
በም.ቅዱ.የሰገነት ኪዳነምሕረት ቤተ ጸሎት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ
ለበለጠ መረጃ፡- 0911-877059 / 0111-572581 / 0920-744622 ጉ/ክ/ከተማ አ.አ. ኢትዮጵያ

Wednesday, June 13, 2018

ለምን ተለያየን ?



ለተከበራችሁ ተመልካቾቻችን የተለያዩ ስብከቶችና መንፈሳዊ አገልግሎቶች በዩቲዩብ እየለቀቅን ስለሆነ ከዚህ በታች ያለውን "YouTube" በመጫን Subscribe በማድረግ ይከታተሉን::

Monday, April 30, 2018

ፍቅር....

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:4-8 - 1 Corinthians 13:4-8
ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር... ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።
Charity suffereth long, and is kind; charity envieth not; charity vaunteth not itself, is not puffed up, Doth not behave itself unseemly, seeketh not her own, is not easily provoked, thinketh no evil; Rejoiceth not in iniquity, but rejoiceth in the truth; Beareth all things, believeth all things, hopeth all things, endureth all things.Charity never faileth: but whether there be prophecies, they shall fail; whether there be tongues, they shall cease; whether there be knowledge, it shall vanish away.

Thursday, April 26, 2018

ትምህርተ ሃይማኖት በምዕራፈ ቅዱሳን

ትምህርተ ሃይማኖት በምዕራፈ ቅዱሳን የሰገነት ኪዳነምህረት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ

ዛሬ ሚያዝያ 16,2010 ዓ.ም በማታው መርሐ ግብራችን ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሊቀ ጳጳስ በቦታው ተገኝተው ቡራኬአቸውን፦በመስጠት አስተምረውናል ደስ ይበላችሁ





ሥርዓተ ምህላ ጸሎት መመሪያ


  1. 150 ዳዊት በማደል ይደገማል፤
  2. የዘወትር ጸሎት በአማርኝ ይደረሰል፤
  3. ወዳሴ ማርያም መልከአ ማርያም መልከአኢየሱስ ይደገማል፤
  4. ተዓምረ ማርያም ይነበብና እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚለው መዝሙር ይባላል፤
  5. አቤቱ ማረን ይቅር በለን 6 ጊዜ ይደረሳል፤
  6. አድህነነ ከማዓቱ ሰውረነ በምህረቱ በእንተ ማርያም ወላዲቱ  6 ጊዜ ይደረሳል፤
  7. ስምአነ አምላክነ ወመድኃኒነ 6 ጊዜ ይደረሳል፤
  8. ኪራላይሶን 6 ጊዜ ይደረሳል፤
  9. እግዚኦ ማሃሪነ ክርስቶስ  12 ጊዜ ከዕጣን ጋር፤
  10. በዕንተ  ማርያም መሃሪነ ክርስቶስ 12 ጊዜ፤
  11. በዕንተ  ሚካኤል  3ጊዜ፤
  12. በዕንተ  ገብርኤል  3ጊዜ፤
  13. በዕንተ  ሩፋኤል ወ ኡራኤል  3ጊዜ፤
  14. በዕንተ  መላዕክት  3ጊዜ፤
  15. በዕንተ  ነቢያት  3ጊዜ፤
  16. በዕንተ  ሐዋርያት  3ጊዜ፤
  17. 17.   በዕንተ   ጸድቃን  ወቅዱሳን  3ጊዜ፤
  18. በዕንተ  ሰማዕታት ወጊዮርጊስ 3ጊዜ፤
  19. በዕንተ ሕጻናት መሃሪነ ክርስቶስ  3ጊዜ፤
  20. ማዕጠንት ይታጠናል ከላኛው እስከ ታቸኛው ወለል፤
  21. ተንስኡ ለጸሎት በማለት ጸሎታ ወንጌል ይጸለያል አራቱ ወንጌል ይነበባል፤
  22. ቅዱስ ተብሎ የሠርክ ኪዳን ይደረስና ይታረጋል፡፡
  23. የንስሐ መዝሙሮች ይዘመራሉ
  24. የ30 ደቂቃ የወንጌል ስብከት ተሰጥቶ 1 ሰዓት ተኩል ይጠናቀቅና ምዕመናን ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ይደረጋል፡፡

ወርሃዊ የልዩ ጉባኤ መርሀግብር

የሃይማኖትዕዉቀትማስፋፊያማህበርየስብከተወንጌልአገልግሎት
ከመጋቢት 1 ቀን 2010 ዓ.ምጀምሮየወጣመርሃግብር
1.  በ3 እና በ16በሊቀትጉኃን መ/ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀልየሚመራ
2.  በ5በመ/ር ሹሜመንግስቴየሚመራ
3.  በ7 እና በ23በሊቀህሩያንየማነብርሃንየሚመራ
4.  በ12መልአከፀሐይቆሞስአባተክለሃይማኖትፀጋዬየሚመራ
5.  በ21በመ/ርዳንኤልአዳሙየሚመራ
6.  በ28 በመ/ር ፍሬቅዱሳንመንክርጥያቄናመልስ
7.  በ29 በመ/ር ገ/ኪዳንከበደየሚመራይሆናል፡፡
ሳምንታዊየሰባክያነወንጌልፕሮግራም
ወርሃዊፕሮግራሙእንዳለሆኖየሳምንቱፕሮግራምእንደሚከተለውይሆናል
በጠዋቱመርሀግብር
1.  መ/ር ዳንኤልአዳሙረቡዕጠዋት
2.  መ/ር ሹምዬመንግስቴሐሙስጠዋት
3.  መ/ር መሪጌታፍሬቅዱሳንአርብጠዋት
4.  መ/ር ገብረኪዳንከበደቅዳሜጠዋት
5.  መልአከፀሐይቆሞስአባ ተ/ሃይማኖትፀጋዬእሁድጠዋት
በማታውመርሀግብር
1ኛ. ረቡዕማታ መ/ር ገብረኪዳንከበደ
2ኛ. ሐሙስማታመሪጌታፍሬቅዱሳን
3ኛ. አርብማታ መ/ር ሹምዬመንግስቴ
4ኛ. ቅዳሜማታሊቀኅሩያንየማነብርሃንገበየሁ
5ኛ. እሁድማታ ዲ/ን አበበተሾመ
የቄደርጥምቀትሲኖርሊቀያየርየሚችልሲሆንተረኛውመድረክመሪይሆናል፡፡

መልካምአገልግሎት!
መጋቢት


ክርስቲያናዊ ስነ-ምግባር 1

የማቴዎስ ወንጌል 25:31-46 - Matthew 25:31-46
የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ጻድቃንም መልሰው ይሉታል። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? ወይስ